የካይዘን ልህቀት ማዕከል የካይዘን ፍልስፍናን ተግብረው በምዘና የላቀ ውጤት ለሚያስመዘግቡ ተቋማት፣ ቡድኖችን እና ግለሰቦች “የኢትዮጵያ ካይዘን ሽልማት” በሚል በየአመቱ የዕውቅና እና ሽልማት ሰነ-ስረዓት ያከናውናል፡፡ ስለሆነም ፍልስፍናውን ተግብራቹ ውጤት ማስመዝገብ የቻላችሁ ተቋማት፣ ቡድኖች እና ግለሰቦች መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡
የመመዝገቢያ ጊዜ፡- ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት
የመመዝገቢያ ቦታ፡- በካይዘን የልህቀት ማዕከል በአካል በመገኘት (አፍሪካ ህብረት ፊትለፊት፤ከትንባሆ ፋብሪካ ወረድ ብሎ የትራፊክ መብራቱ ጋር ሳይደርሱ) ወይም በኢሜል አድራሻ፡- dere1684@gmail.com
ለበለጠ መረጃ፡- 0987852326
ማሳሳቢያ

    • በምዝገባ ወቅት በካይዘን ትግበራ የተገኘ ውጤትን የሚያሳይ ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ሪፖርት ይዞ መገኘት ወይም መላክ (የሪፖርት መላኪያ ቅጽን ከላይ ባለው አድራሻ በመጠቀም ማግኘት ይቻላል)
    • የካይዘን ትግበራን ቢያንስ ለስድስት ወር ተግብሮ ውጤት ማስመዝገብ የቻለ ተቋም መሆን አለበት

የካይዘን ልህቀት ማዕከል