Loading...

የኢከኢ የ2011 መጀመሪያ ግማሽ ዓመት ሪፖርት በኢፌድሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን

//የኢከኢ የ2011 መጀመሪያ ግማሽ ዓመት ሪፖርት በኢፌድሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን

ኢንስቲትዩቱ በመጀመሪያው ግማሽ በጀት ዓመት ከ45 ሚሊዮን ብር በላይ ከብክነት ማዳኑን አስታወቀ

Ethiopian Kaizen Institute Civil service 6 month evaluation

የኢትዮጵያ ከይዘን ኢንስቲትዩት የ2011 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት ሪፖርቱን ለሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አቅርቧል፡፡ የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ጥር 07/2011 ዓ.ም በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አዳራሽ በተደረገ የግማሽ ቀን የግምገማ መድረክ ተሳትፈዋል፡፡ በግማሽ ዓመቱ አገልግሎት በሰጣቸው ተቋማት ከአርባ አምስት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሽህ ብር በላይ (45,801,983.61 ብር) ከብክነት ማዳን መቻሉ ታውቋል፡፡ በተጨማሪም 4,116.78 ካሬ ሜትር ነጻ ቦታ ማግኘት ተችሏል፡፡

ሪፖርቱን ያቀረቡት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ያኢ እንዳሉት በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ከይዘንን ከተገበሩ ተቋማት 15,958,335.25 ብር፤በአገልግሎት ዘርፍ ከይዘንን ከተገበሩ ተቋማት 27,112,131.16 እና በአቅም ግንባታ ዘርፍ ተሰማርተው ከይዘንን በተገበሩ ተቋማት ደግሞ 2,731,517.20 ብር ነው ከብክነት ማዳን የተቻለው፡፡

በግማሽ ዓመቱ የመጀመሪያ ደረጃ ከይዘን ትግበራ የጀመሩ ተቋማት 80 ሲሆኑ የሁለተኛ ደረጃ ከይዘን ትግበራ የጀመሩ ተቋማት ደግሞ 7 ናቸው፡፡ የኢንስቲትዩቱ የደንበኛ እርካታም 89.2 ከመቶ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ በግማሽ ዓመቱ የኢንስቲትዩቱ አማካይ አፈጻጸም 79.43 በመቶ ላይ መሆኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ በዛብህ ወልደየስ እንዳሉት ኢንስቲትዩቱ በ6 ወራት ውስጥ ያስመዘገባቸው ውጤቶች ጉልህ ናቸው፡፡ በቀጣይም የትኩረት ነጥቦችን ለይቶ በመንቀሳቀስ የበለጠ ውጤታማ ሊሆን የሚችልበትን አሠራር ዘርግቶ እንዲንቀሳቀስ ኮሚሽነሩ አሳስበዋል፡፡

By |2019-01-24T09:24:24+00:00January 23rd, 2019|ዜና|0 Comments

About the Author:

Leave A Comment