Loading...

የከይዘን አመራር ፍልስፍና ምንነት

ከይዘን የራሱ የሆኑ መርሆዎችና ቴክኒኮች ያሉት የአሠራር ፍልስፍና ነው፡፡ የከይዘን አመራር ፍልስፍና ቀጣይነትና ተከታታይነት ያለው የተሻለ ለውጥ ማምጣት ላይ የተመሠረተ ሲሆን ፍልስፍናው ከሁሉም በላይ የአመለካከት ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ነው፡፡ነባራዊ ሁኔታን በመረዳት አመራሩንና ሠራተኛውን አሳታፊ በማድረግ ለለውጥ.ለጥራትና ምርታማነት ንቅናቄ ያነሳሳል፡፡ዋና ለውጥ ተዋናይ አድርጎ የሚወስደው የሰው ኃይሉን በተለይም ፈጻሚውን ሲሆን ሠራተኛው በከይዘን አመራር ፍልስፍና በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው በማድረግ ቀጣይነት ያለው የተሻለ የለውጥ ሥራን በንቃት ተሳታፊ እንዲሆን ማስቻል ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡

ስለከይዘን ለመረዳት በቅድሚያ በጃፓን በሂደት የዳበሩ የሥራ አመራር እንዲሁም የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ ዘዴዎችን ከመሠረቱ መገንዘብን ይጠይቃል፡፡ጃፓን ኢንዱስትሪዎቿን ያሳደገቻቸው በአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪ ልማት ላይ ትኩረት ሰጥታ በመስራቷ ሲሆን ለዚህም የከይዘን አመራር ፍልስፍና በእጅጉ ጠቅሟታል፡፡ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ጃፓን ለዓለም ገበያ ታቀርባቸው የነበሩ ምርቶች ጥራት አሜሪካና አውሮፓ ከሚያመርቷቸው ምርቶች ጋር ሲነጻጸር በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ በዓለም ገበያ ላይ ተወዳዳሪ መሆን አልቻለችም ነበር፡፡ይህንን ችግሯን ለመፍታት ከሌሎች ሀገሮች ለመማር በተለያዩ የሙያ መስኮች የተሰማሩ ምሁሮቿን ወደ አውሮፓና አሜሪካ በመላክ የእነዚህን ሀገሮች አሠራርና ቴክኖሎጂ በመቅሰምና በመቀመር ከራሷ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማጣጥምና ዜጎቿም ተግተው በመስራት የራሳቸውን የከይዘን አመራር ፍልስፍና በመቀመር በጥራትና ምርታማነት ላይ የተመሠረተ ፈጣን የቴክኖሎጂና የኢኮኖሚ ልማት በማስመዝገብ በአሁኑ ወቅት ከበለጸጉ ግንበር ቀደም ሀገራት አንዷለመሆን አስችሏታል፡፡

ከይዘን ምርትና አገልግሎትን ተወዳዳሪና ውጤታማ በማድረግ የጋራ ተልዕኮን ከማሳካት አኳያ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሩን እንዲሁም ሠራተኞችን በማስተሳሰር ሰው በማንኛውም ቦታ እና ጊዜ ለውጥና መሻሻልን አስቦ እንዲንቀሳቀስ የሚያደርግ፣ፈጠራና አዲስ አስተሳሰብን የሚያበረታታና ሰፊ የለውጥ፣ የጥራትና የምርታመነት ንቅናቄን በመፍጠር ስኬታማ የሚያደርግ የአመራር ፍልስፍና ነው፡፡

ስለሆነም የከይዘን የተሟላና የተቀናጀ የአሳታፊነት ባህርይ ለሀገራችን የለውጥ አመራር እና ልማታችንን ለማፋጠን የበለጠ ተስማሚ ነው፡፡

ስለከይዘን የአመራር ፍልስፍና በተሟላና በተብራራ መልኩ የጻፋት ማሳኪ ኢማይ የተባሉ ጃፓናዊ ምሁር ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ በ198ዐዎቹ አጋማሽ ላይ ሆነው ጃፖን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ በኋላ የገጠማትን የጥራትና ምርታማነት ችግሮች በከይዘን የአመራር ፍልስፍና አማካኝነት እንዴት ለመወጣት እንደቻለችና በዓለም ደረጃ ጠንካራና ተወዳዳሪ ኢኮኖሚና ማኅበረሰብ ለመፍጠር እንዴት እንደተሳካለት ‘’KAIZEN: The Key to Japan’s Competitive Success’’ በተሰኘው መጽሐፋቸው አብራርተዋል፡፡

በመጽሐፋቸው መግቢያ ላይ “የከይዘን ተግዳሮት” በሚለው ርዕስ ስር የከይዘን ፍልስፍና መለያው ከፍተኛውንና መካከለኛውን አመራርና ሠራተኛ ያሳተፈ የማያቋርጥ ለውጥና መሻሻል መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ የከይዘን አስተሳሰብ በሁሉም ጃፓናዊ አእምሮ እንዲሰርጽ በመገናኛ ብዙኃን (በጋዜጣ፣በቴሌቪዥንና በሬዲዮ) ሰፊ ሥራ የተሠራ ሲሆን በመንግስት ባለሥልጣናት፣ በፖለቲከኞች እና በዲፕኘሎማቶች ሁልጊዜ የሚነገርለት የአመራር ፍልስፍና መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ የጃፖን ህዝብ ከህጻንነት ጀምሮ በዚህ ፍልስፍና ተቀርጾ ያደገ ነው፡፡

ኢማይ በዚሁ ርዕስ ስር የመጽሐፋቸው ጭብጥ የሆነውን የከይዘን ፍልስፍና ምንነት እንዲህ ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ‘’ KAIZEN is the basic philosophical underpinning for the best in Japanese Management…. It is a unifying thread running through the philosophy, the systems, and the problem solving tools developed in Japan over the last 30 years’’

ከዚህ ሃሣብ የምንረዳው ከይዘን የራሱ ሶስት ዋና ዋና ምሰሶዎች እንዳሉት ነው፡፡ እነሱም የአመራር ፍልስፍና፣የአሠራር ሥርዓቶችና ቴክኒኮች ናቸው፡፡

By |2019-02-13T20:17:56+00:00February 13th, 2019|የመጀመሪያ ደረጃ ከይዘን|0 Comments

About the Author:

Leave A Comment