Loading...

መሠረታዊ የከይዘን ቴክኒኮች

7ቱ ብክነቶች (7 Muda)

ሙዳ (Muda)

በአንድ ኢኮኖሚ ውስጥ ቁሳዊ ሀብት ለማምረት የዋለ ሥራ ምርታዊ ሥራ (Productive Labour) ይባላል፡፡ በማንኛውም ምርታዊ ሥራ ውስጥ ደግሞ ፋይዳ የሌው ፣ለምንሰጠው አገልግሎት ወይም ምናመርተው ምርት ምንም ዓይነት የጥራትም ሆነ የብዛት ውጥ የማያመጣ፣ የስራ ሂደትን የሚያዘገይ(አን የሚይዝ)፣በአመራረት ላይም ወጪ የሚጨምር ማንኛውም አላስፈላጊ ነገር በጃፓንኛ ሙዳ(Muda) ሲሆን በአማርኛ ደግሞ ብክነት ይባላል፡፡በአጠቃላይ ብክነት(ሙዳ) በምርታዊ ስራ ት ውስጥ የማያስፈልግ ወይንም ሴት የማይጨም አሠራር ነው፡፡

ብክነት (Muda) የማምረቻ ዋጋ እንዲጨምር እና የምርት ጥራት እንዲቀንስ ከሚያደርጉ ምክንያቶች አንዱ ነው፡፡ በማምረት ሂደትም ሆነ ተሠርተው ከተጠናቀቁት ምርቶች ውስጥ የጥራት ደረጃቸውን ሳያሟሉ ይቀራሉ፤እነዚህንም እንደገና ለመሰራት (ለማስተካከል) ተጨማሪ ወጪ፣ጉልበትና ጊዜ ይጠይቃል፡፡ እንዲሁም የተመረተው ምርት በተፈለገበት ጊዜና ቦታ በወቅቱ ስለማይደርስ ከደንበኛ ጋር ያለውን ግንኙነት ያሻክራል፡፡

የሙዳ አይነቶች

ሀ) ከሚያስገው በይ ማምረት (“Muda” of Overproduction)

ምርት በአይነት፣ በመጠን፣ በይዘት እና በጊዜ ተጠቃሚዎች ወይም ደንበኞች ከሚፈልጉት በላይ ሲመረት የሚፈጠር የብክነት ዓይነት ነው፡፡ ለዚህ ብክነት መፈጠር መንስኤዎቹ በአመራረት ሂደት ውስጥ የሰው ኃይና የማሽኖች የማምረት አቅም አመመጣጠንየሰው ሀይል ሀብትና ማሽን ከሚፈለገው በላይ ሆን እና ብቃትና ጥራት ባለው የገበያ ስርዓት (marketing management) አለመመራት ናቸው፡፡ በተጨማሪም በገፍ ማምረት(ምርትን በይ በዩ ማምረት ዘዴ) እና ያልተደላደለ የአመራረ ስልት ይጠቀሳሉ፡፡

ገበያተኛን የማወቅ፣የማግኘት፣የማበራከትና ቋሚ የማድረግ ጥረት ምርትን ወይም አገልግሎትን ለማዘጋጀት ከሚደረግ ጥረት ያላነሰ ትኩረትን ይጠይቃል፡፡የገበያ ስርዓት (marketing management)፣ የገበያ ፍላጎት (Demand) እንዲሁም የተቋሙ የማቅረብ ችሎታ (Supply)ምን ያህል እንደሆነ ማጥናት ያስፈልጋል፡፡ ከሚፈገው በይ ማምረት (“Muda” of Overproduction) የሚያስከትቸው በርካታ ችግሮች አሉ፤የማስረከቢያ ጊዜን የማራዘም፣ለንብረት ቁጥጥር በቂ የግንዛቤ እጥረት እና ዝግጁ አለመሆን፣የቦታ ብክነትየማጓጓዝ እና የፍተሻ ሥራዎች መብዛትቀጣይ የውጥ ስራዎችን ማከምየካፒታል መባከን (መያዝ)እንዲሁም ሥራ ማስኬጃ የሚያስፈልገውን ወጪ መናርን ያስከትላል፡፡

ለ) የንብረት ክምችት ብክነት (“Muda” of Inventory)

ለማምረት የሚያስፈልጉ በመጋዘን ውስጥ የሚቀመጡ ጥሬ ዕቃዎች፣ምርቶች፣መለዋወጫዎች፣ያለምንም አገልግሎት በመጋዘን የተከማቹ መሳሪያዎችና መገልገያዎች የሚፈጠር ጉዳይ የንብረት ክምችት ብክነት ይባላል፡፡ በስራ ፍሰት (በምርት ሂደት) ውስጥም የንበረት ክምችት ብክነት ይፈጠራል፡፡ ያለበቂ ጥናት እና እውቀት መሰረት ባላደረገ ትንበያ ማምረት፣በስራ ክፍሎች መካከል ባለመናበብ ማምረት፣ብዙ ክምችት መያዝ የሚያመጣቸውን ችግሮችአለመገንዘብ እንዲሁም ስርዓት የሌለው አቀማመጥ (Lay out)፣ወደፊት የምርት እጥረት ያጋጥማል በሚል እምነት በብዛት ማምረት፣ወዘተ ለንብረት ክምችት ብክነት መፈጠር ዋና ዋና መንስኤዎች ናቸው፡፡

የንብረት ክምችት ብክነት አንድን ተቋም ወደኪሳራ ሊወስደው ይችላል፡፡ ምርት ከሚፈለገው በላይ ሲከማች ገንዘብ ስለሚይዝ አገላብጦ ሊሰራበት አይችልም፡፡ በክምችት ላይ ያለው ምርት ሰፊ ቦታ ይይዝበታል፡፡ የምርቱ መጠቀሚያ ጊዜው ስለሚያልፍ ሊበላሽ ይችላል፡፡በተጨማሪም የማሽኖችና የሰዎችን አቅም መገመት ያግታ፡፡ የንብረት ቁጥጥር ለማድረግ ጊዜ ከመውሰዱም በላይ የማምረት ሂደቱ ቀልጣፋ እንዳይሆን ያደርጋል፡፡

ሐ) የመጠበቅ ብክነት (“Muda” of Waiting)

ይህ ብክነት አይነት በማምረት  ላይ በቅብብሎሽ ሰንሰለት ውስጥ በመዘግየት ይከሰታል፡፡ ዕቃን፣ አሰራርን፣ ማጓጓዝን እና ፍተሻን የመጠበቅና ቅሚያ አለመስጠትን ያጠቃልላል፡፡ የመጠበቅ ብክነት(“Muda” of Waiting) መንስኤዎች በማምረት ሂደት ውስጥ የሚያጋጥሙ ማነቆዎች ሲሆኑ በምርት መሳሪያዎች፣በጥሬ ዕቃዎች፣በአሠራር ዘዴዎችና በሰው ኃይል ድክመት፣መሽኖችን በጥራትና በብቃት ለመተከል (Lay out problem )፣የማሽንም ሆነ የሰው ሀይል አቅም አመመጣጠን፣የግብአት አቅርቦት እጥረት፣ የባለድርሻ አካላት የጠበቀ ቅንጅት እና ትስስር አለመኖር፣የባለሙያዎች አቅም ውስንነትና በሌሎችም ምክንያቶች ይፈጠራል፡፡

መ) የማጓጓዝ ብክነት (“Muda” of Transportation)

የማጓጓዝ ብክነት (“Muda” of Transportation) የሚፈጠረው በምርት ሥራ ሂደት ውስጥ ግብዓትንና ምርትን እሴት ቆጣቢ ባልሆነ መንገድ ለማጓጓዝ ጉልበትን፣ወጪንና ጊዜ በማባከን ነው፡፡ የማጓጓዝ ብክነት የሚያጋጥመው ዘመናዊ የሆኑ የመጓጓዣ ዘዴዎችን ከማምረቻው ጋር ግንኙነት ያላቸውን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና ማሽኖችን ካለመጠቀም ነው፡፡በተጨማሪም ይህ ብክነት የሚያስከትለውን ጉዳት ካለመገንዘብ እና የማምረቻ ቦታዎችን የቦታ አቀማመጥ፣ምርትንና ግብአትን ቀልጣፋና ለስራ አመች በሆነ ዘዴ ካለማደራጀት ይከሰታል፡፡

በቂ ጥናት ባልተደረገበት መንገድ ማጓጓዝ የማጓጓዝ ብክነት (Muda of Transportation) ሊያጋጥም ይችላል፡፡ በምርታማነት ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖም ቀላል አይሆንም፡፡ የማጓጓዝ ብክነት (Muda of Transportation) የሚያስከትቸው ችግሮች በርካታ ቢሆኑም ጥቂቶቹ፤የጉልበትና ገንዘብ ብክነት፣ዝቅተኛ የሥራ ፍሰት፣የማሽን መሰናከል፣የቦታ ጥበት ፣የምርታማነት መቀነስ፣የምርትና የግብዓት ብልሽት እና የማምረቻ ጊዜ መራዘም ናቸው፡፡

ሠ) የማምረት ግድፈት ብክነት (“Muda” of Defect-Making)

የማምረት ግድፈት ብክነት (“Muda” of Defect-Making) የሚፈጠረው በማምረት ሂደት ውስጥ ከሚመረተው ውስጥ የጥራት ደረጃውን ሳያሟላ በሚመረት ምርት ላይ ነው፡፡ ይህም የሚከሰተው በምርት ሂደት ውስጥ ተሟ የጥራት ቁጥጥር (ፍተሻ) ሲደረግ እና ብዙ ለማምረት በሚደረግ ደረጃውን ያጠበቀ አሰራር (Lack of standard operation) ነው፡፡

ግድፈት (ሽትው ምርት የማምረት ብክነት መንስኤዎች በምርት ሂት መጨረሻ ይ ብቃት እና ጥራት ያለው ፍተሻ አለማድረግ፣ምርትን በገፍ ለማምረት በሚደረግ ጥረት ግድፈት ወይም ብልሽት መፈጠሩ፣ ደረጃውን ያጠበቀ አሰራር (Lack of standard operation) መከናወኑ እና ሌሎችም ናቸው፡፡ አምራቱ ግድፈት ወይም ብልሽት ያለው ምርት ሲያመርት ምርቱ በገበያ ላይ ተቀባይ ስለማያገኝ እንደገና ለማምረት (ለማስተካከል) ይገደዳል፤በዚህም የድርጅቱ ወጪ ይንራል፡፡ በአምራቹና በደንበኛው መካከልም ቅሬታ ይፈጠራል፡፡

ረ) የእንቅስቃሴ ብክነት (“Muda” of Motion)

በማንኛውም ጊዜ፣ቦታና ሁኔታ ስራን ለመስራትም ሆነ ለማምረት እንቅስቃሴ (Motion) ያስፈልጋል፡፡ነገር ግን በስራ ቦታ ላይ የሚደረግ አላስፈላጊ ወይም እሴት የማይጨምር (Non value) እንቅስቃሴ ከሆነ የእንቅስቃሴ ብክነት ይባላል፡፡የእንቅስቃሴ ብክነት(“Muda” of Motion) መንስኤዎች የሚባሉት ውስብስብ የአሰራር ስልት፣ደረጃውን ያልጠበቀ የአሠራር ቅደም ተከተል፣ያልተስተካከለ የማሽን አተካከል እና ትክክለኛ ያልሆነ የሰራተኛ አቀማመጥ ወይም አቋቋም የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ የእንቅስቃሴ ብክነት( “Muda” of Motion) የሚያስከትላቸው በርካታ ችግሮች ቢኖሩም፤የሠራተኛን ሙያ መቀነስየሰው ኃይና የሥራ ሰዓት መጨመርተረጋጋ አሰራር፣የማምረቻ ጊዜን ማራዘም እና በባለሙያ ላይ የአካል ጉዳት ማስከተል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ሰ) የአሠራር ብክነት (“Muda” in Processing)

ይህ ብክነት ዓይነት የማያስፈጉ አሰራሮችን በማከናወን የሚፈጠር ነው፡፡ ተጠቃሚው ከሚፈልገው ደረጃ በላይ አላግባብ የሚያከናውን ሲሆን በስራ ሂደት የሚፈጠሩ ግድፈቶችን ለማስተካከል የሚያስፈልግ ወጪን ያጠቃልላል፡፡ የአሠራር ብክነት (“Muda” in Processing) መንስኤዎች የሂት ቅም ተከተችን ተንትኖ ያማወቅየሂቶች ይዘት ተንትኖ አለመገንዘብ፣ትክክኛ መሳሪያዎችን በተገቢው ቦታ አለመጠቀም፣ያልተላ የደረጃ ወሰን(መደብ)፣ ከዚህ ሌላ አሰራር እንደሌለ አድርጎ ማሰብ፣አላስፈላጊ የሰው ኃይል፣የሥራ ጊዜን ማራዘም እና ፈቶችን ማብዛት ናቸው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ

By |2019-02-13T20:32:10+00:00February 13th, 2019|የመጀመሪያ ደረጃ ከይዘን|0 Comments

About the Author:

Leave A Comment