የአማካሪዎች የብቃት ማረጋገጫ ምዘና (CARS) ምዝገባ ማስታወቂያ

                         10/09/2014

የካይዘን ልህቀት ማዕከል የካይዘን የአማካሪዎች የብቃት ማረጋገጫ ምዘና (CARS) ከኢትዮጵያ ኢንዱስትሪያል መሀዲሶች ማኅበር ጋር በመተባበር በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

በመሆኑም የካይዘን ስራ አመራር ፍለስፍናን በማሰልጠን፣ በማማከር እና በመተግበር ላይ ያላችሁ እና በመሰረታዊ ካይዘን (Basic kaizen) ንዲሁም በመካከለኛ ደረጃ ካይዘን (Intermediate kaizen) የአማካሪነት የብቃት ማረጋገጫ ምዘና ለመውሰድ ፍላጎት ያላችሁ ባለሙያዎች ከ10/09/2014ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 20 ቀናት ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ በኦንላይን ብቻ አስፈላጊውን መረጃ በማስገባት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

 ለካይዘን ልህቀት ማዕከል አማካሪዎችና ተመራማሪዎች የመመዝገቢያ ሊንክ http://192.168.0.139/carsap ሲሆን ለተለያዩ መንግስታዊና የግል ተቋማት ባለሙያዎች የመመዝገቢያ ሊንክ http://196.188.64.39/carsap ነዉ፡፡

ማስታወሻ

  • ተመዛኙ ከምዘና ቀን በፊት የመመዝገቢያ ክፍያ (registration fee) ለመሰረታዊ ካይዘን  ብር 300 (ሦስት መቶ)  እና ለመካከለኛ ደረጃ ካይዘን ብር 400 (አራት መቶ) በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪያል መሃዲሶች ማኅበር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000198179764 በማስገባት የተከፈለበትን ደረሰኝ በፈተናው ቀን ይዞ መገኘት ይኖርበታል፡፡
  • የፅሁፍ ምዘና የሚሰጥበት ቀን ለመሰረታዊ  ካይዘን ሰኔ 04/2014 . ጧት 300 ሰዓት  ሲሆን  ለመካከለኛ ደረጃ  ካይዘን ሰኔ 04/2014 . ከሰአት በኋላ 800 ሰዓት ነው፡፡
  • የፅሁፍ ምዘና ቦታ  ካይዘን ልህቀት ማዕከል  አጠገብ በሚገኘው በምርታማነት ማዕከል ነው፡፡
  • የቃል መጠይቅ ምዘና የሚሰጥበት ቀን እና ቦታ በኢሜል እና በስልክ የሚገለፅ ይሆናል፡፡

ካይዘን ልህቀት ማዕከል                                                           ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0913786725/0987852326 መደወል ይችላሉ፡፡